EBOOK

ከርሞ ልጅነት

Yitbarek Mengistu
(0)

About

የመጽሐፉ ዋና ገጸ-ባህርይ ይትባረክ መንግስቱ ፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ተወልዶ በእምነት የተቀረጸ ሕይወቱን በዚህ አስደናቂ መጽሐፍ ውስጥ በጥልቀት ይተርካል። አባታቸው ሲሞት ይትባረክ ገና በልጅነቱ የአባትነትን ኃላፊነት ሸፍኖ ያለ ባል የቀሩት እናቱን ፣ ሁለት ወንድሞቹንና እህቱን ለመርዳት የሄደበት ርቀትና የከፈለው ዋጋ ጥንካሬውን ፣ ማንነቱን እና እምነቱን በኃይል ፈትኖበታል።

መጽሐፉ ከኑሮ ፈተና ፣ ከማንነት ፍለጋ፣ ከስደት፣ ከአባትነት እና ከመንፈሳዊ ንቃት ጋር የተያያዘውን የሕይወቱን እውነተኛ ጉዞ በሚያስደንቅ መልኩ ያቀርባል። በህይወት አጣብቂኝና በብዙ ተግዳሮት የተሞላው ውስብስብ የልጅነት ጅማሬውን ፣ እስከ ወጣትነት አልፎም እስከ ቤተሰብ ኃላፊነት የሚደርስ ጉዞውን እያዋዛ ያጫውተናል። የሰውን ነፍስ በህይወት ሂደት ውስጥ በስውር የሚቀርጹትን ያልታዩትን ሞራጅ ፈተናዎችንም ይገልጣል።

ደራሲው በቅንነት የወንድነትን እና የአባትነትን ትርጉም ፣ የቤተሰብ ዋናነትን ፣ ያልተመለሱ ጸሎቶችን እና የዝምታን ሚስጥር እንዲሁም ለመሞት ያልፈቀደ ጽናት የወለደውን ተስፋ በደንብ ይመረምራል። ይህ እጅግ የተበላሹ ከሚመስሉ የልጅነት ጅማሬዎች የተነሳው የይትባረክ ታሪክ ፤ በሂደት ከህይወት ፈተና እና ስቃይ ውስጥ ልምድን እና ጥበብን ፣ ከጥርጣሬ ውስጥ ደግሞ የሚያጸና እምነትን ማፍለቅ ችሏል።

ባለ ታሪኩ የህይወትን ተግዳሮት ወደ መጻኢ እድል ለመቀየር እምነትን ፣ ተስፋን እና ፍቅርን በአንድ ላይ ገምዶ በየፈርጁ እንዴት እንደሚታገል በግልጽ ያሳየናል። ይህ መጽሐፍ እውነተኛ ስብእናውን እና የህይወት ስፍራውን በህይወት ፈተና ውስጥ ያገኘ የአንድ የአስደናቂ ሰው እውነተኛ ታሪክ ነው።

ይህ በተለያዩ ባህሎችና በአህጉራት ጭምር የሚንቀሳቀስው ታሪክ የግል ተሞክሮ ብቻ አይደለም ፤ ይልቁንም አንባቢ ስለ ህይወት ዓላማው እና በህይወት ውስጥ ስላለው ድርሻ ከልቡ እያሰበ እራሱን እንዲያይበት የሚያደርግ አንጸባራቂ መስታወት ነው።

Related Subjects

Artists