EBOOK

Jesus Our Salvation

በነፍሳችን ድነት ውስጥ ያለው የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት

F. Wayne MacLeod
(0)

About

ብዙ ጊዜ መዳናችን በሕይወታችን የተፈጠረ አንድ ክስተት አድርገን እንናገራለን፡፡ አንዳንድ አማኞች ሕይወታቸው የተቀየረበትን ጊዜ እና ሁኔታ እንኳን ሊጠቁሙ ይችላሉ። ያ ክስተት አስደናቂ ቢሆንም መዳን ከተሞክሮ ይልቅ ለአንድ ሰው የበለጠ ትርጉም እንዳለው ልናገር እወዳለሁ። ጌታ ኢየሱስ የሚሰጠን ደህንነትን ብቻ ሳይሆን እርሱ ራሱ መዳናችን ነው ወደሚለው ሃሳብ እመጣለሁ።

ያለ ጌታ ኢየሱስ መዳናችን አውን ሊሆን አይችልም ነበር። በዚህ ሂደት ውስጥ በማንኛውም ጊዜ የክርስቶስን ማንነት ካስወገድን ያለ ተስፋ እንጠፋለን። እርሱ የኃጢአታችን ዋጋ ነው። እርሱ በአብ ዘንድ እንድንቆም የሚያደርገን ድፍረታችን ነው። እርሱ የክርስትናን ሕይወትን ለመኖር የሚያስችለን ኃይላችን ነው። ስለ መዳን ስንናገር የጌታ ኢየሱስን ማንነት እናያለን።

በዚህ ጥናት ኢየሱስ ክርስቶስ መዳኛችን መሆኑን ለመመልከት ጊዜ እወስዳለሁ። ዓላማዬ እያንዳንዱ የማንነታችን ገጽታ በእርሱ ብቻ እንደሚገኝ ማሳየት ነው።

Related Subjects

Artists