EBOOK

የመንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ

Ermias Tilahun
(0)

About

መንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ ነው፤ ከአንድ የአመለካከት፣ የሕይወት፣ የባሕሪ፣ የአቅም፣ የብስለት የራእይ ደረጃ ወደ ሌላ የአመለካከት፣ የሕይወት፣ የባሕሪ፣ የአቅም፣ የብስለትና የራእይ ደረጃ የሚደረግ ጉዞ። ለዚህ ዓይነቱ ጉዞ ቀጥተኛ ምሳሌ እንዲሆነን እግዚአብሔር ዘጸአት የተባለ የዕብራውያንን የጉዞ ዘገባ የያዘ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲቀመጥልን አድርጓል። በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ውስጥ ከሌለን፣ ሕይወታችን ወደ ሃይማኖታዊነት ያሽቆለቁላል። ሕያው የሆነ የክርስትና ሕይወት ይዘት እንዳለን የሚታወቀው በምናደርገው የወደፊት ተራማጅ ግስጋሴ ነው። ጉዞ ካለ እንቅስቃሴ፣ እርምጃ፣ መሻሻል፣ እድገት፣ ተጽዕኖ፣ ግብ ይኖራል። እነዚህ እሴቶች (values) ለሕይወታችን እጀግ አስፈላጊ ቅመሞች ናቸው። ይህ መጽሐፍ የክርስትና ሕይወታችን እንቅስቃሴ፣ መሻሻል፣ እድገት፣ ተጽዕኖና ግብ እንዲኖረው ለማገዝ የተጻፈ ነው። እንዲህ ዓይነቱ ሕይወት በሌላ ቋንቋ የደቀመዝሙርነት ሕይወት ተብሎ ይታወቃል። የዚህ መጽሐፍ ጽንሰ ሐሳብ የደረጀው በዚህ የደቀመዝሙርነት ሕይወት ጅማሬ፣ ሂደት፣ ተግዳሮትና ግብ ላይ ነው።ጉዞ ወይም በመንፈሳዊ ሕይወታችን ግስጋሴ የምናደርገው ከጌታ ጋር ባለን መለኮታዊ ግንኙነት ነው። ይህ አነስተኛ መጽሐፍ ሁለት ክፍሎችና አራት ምዕራፎች አሉት። የመጀመሪያው ክፍል መለኮታዊ ግንኙነትን የሚያሳዩ ሁለት ምዕራፎች ሲኖሩት፣ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ በመለኮታዊ ግንኙነት ውስጥ መዋልን የሚያሳዩ ሁለት ምዕራፎች አሉት። መንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ ስለ ሆነ፣ በዚህ መጽሐፍ ጌታ ኢየሱስ ያደረጋቸውን ሁለት ጉዞዎች ወስደን የሚጠቅሙንን መርሖች እንመለከታለን። አንደኛው ጉዞ ጌታ ኢየሱስ በወላጆቹ ቤት እያለ በአሥራ ሁለት ዓመቱ ያደረገው ጉዞ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በአገልግሎቱ ዘመን ጅማሬ ላይ በሠላሳ ዓመቱ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ያደረገው የመጀመሪያ ጉዞ ነው። ሁለቱም ጉዞዎች ለሕይወታችንና ለመንፈሳዊ ልምምዳችን ትልልቅ መንፈሳዊ መርሖችን የምንማርባቸው ናቸው። የመጀመሪያው ጉዞ ከጌታ ጋር ያለንን ግንኙነት ሲያመለክት፣ ሁለተኛው ጉዞ ደግሞ ከጌታ ጋር አብሮ የመዋልን አስፈላጊነትና ተግዳሮቱንም ያሳየናል። በመጀመሪያው ክፍል የመጀመሪያውን ጉዞ፣ ማለትም በአሥራ ሁለት ዓመቱ ያደረገውን ጉዞ እንመለከታለን፤ በሁለተኛው ክፍል ደግሞ በሠላሳ ዓመቱ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ያደረገውን ጉዞ እንመለከታለን። መልካም ንባብ!

Related Subjects

Artists