EBOOK

About
ድህነት የገንዘብ እጥረት ሳይሆን የአስተሳሰብ ችግር ውጤት ነው። ብዙ ገንዘብ ኖሯቸው ከድህነት አስተሳሰብ ግን ያልተላቀቁ ብዙ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች ምንም እንኳ የገንዘብ እጥረት ባይኖርባቸውም አስተሳሰባቸው ውስጥ ያለው ድህነት ስላልተሸነፈ፤ ይህ ድህነት ከሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት፣ በባህሪያቸው፣ በስብእናቸውና በተለያየ መልኩ ይገለጣል። ስለዚህ ድህነት የገንዘብ ድህነት ብቻ ሳይሆን የባህሪ ድህነት፣ የአስተሳሰብ ድህነት፣ የስብእና ድህነት፣ የግንኙነት ድህነት፣ የባህል ድህነት፣ ወ.ዘ.ተ ተብሎ ሊዘረዘር ይችላል። ከእነዚህ ሁሉ ግን መሰረታዊው ነገር የአስተሳሰብ ድህነት ነው። አስተሳሰባችን ውስጥ ድህነት ካለ በኢኮኖሚ አቅማችን እንኳ እጥረት ባይኖርብን፤ ከድህነት ተጽእኖ ውጭ ግን አይደለንም። ድህነትን ከአስተሳሰባቸው ማስወገድ የቻሉ ከኢኮኖሚያቸው ድህነትን ማስወገድ ያን ያህል ከባድ አይሆንባቸውም። ምክንያቱም የኢኮኖሚ ድህነትም ቢሆን፤ መነሻ መሰረቱ የአስተሳሰብ ድህነት ነው። (ከመጽሐፉ የተወሰደ)ደራሲው ከዚህ በፊት 'በትምህርት ስኬታማነትን የሚያጎናጽፉ መርሆች' በሚል ርእስ የጻፈው መጽሐፍ ተማሪዎች በትምህርታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረው ይታወቃል።