EBOOK

About

ይህ በዘፍጥረት 4:16 የሚገኝ ቀለል ያለ ጥናት ነው። በዘፍጥረት 4:16 ውስጥ የሚገኘው የቃየን ታሪክ በበርካታ መንገዶች የእኛም ታሪክ ነው። ስለ ሰው አመጽ እና ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቶ ስለ መኮብለል የሚናገር ታሪክ ነው። ቃየን ከእግዚአብሔር ፊት የወጣበትን ታሪክ ስንመለከት እኛም ሸሽተን ለመሄድ ያለብንን ፈተናዎች እናውቃለን።

በዚህ ዓለም መስህቦች እና ኃጢአተኛው ልባችን ምን ያህል እንደምንፈተን እናውቃለንና።

ሆኖም ይህ ምንባብ፤ከቃየን የአመጽ ታሪክ ያለፈ ነው። ለሕዝቡ ያለው የእግዚአብሔር ልብ መገለጠ ነው። የተፈጠርነው በኤደን ገነት ውስጥ እንድንኖር ነበር። ኃጢአት የገነትን በረከቶች የመለማመድ እድል ባሳጣን ጊዜ፤ጌታ ኢየሱስ ይህንን እድል በሞቱ እና በትንሳኤው መልሶ ሰጠን። በረከቶቹ እና እድሎቹ በጌታ ኢየሱስ የቀረበውን ይቅርታ ለሚቀበል ሁሉ እንደገና ቀርበዋል።

ጸሎቴ እንደገና በእግዚአብሔር ህልውና ደስታ እና የበረከቱ ሙላት ስፍራ ውስጥ ለመኖር እንዲያነሳሳን ነው።

Related Subjects

Artists